መቼም በፌስቡክ ላይ ብዙ አይነት ነገሮችን ከሰሞኑ እንመልከታለን። በዚህ የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ቀልቤን ከሳበው ትልቅ ነገር የካሱ ገረመው ፎቶ ነበር። ይህ ብላቴኔ በኮንሶ የሚኖር ታዳጊ ሲሆን በሰፈሩ ከኮንሶ ያቤሎ የመንገድ ስራ ላይ ኤክስካቫተር፤ ግሬደር እና ገልባጭ መኪኖችን በመንገድ ስራ ሲመላለሱ ተመልከተ። በዓይምሮው እሱ ምን መስራት እንድሚችል በመረዳት ኤክስካቫተር በካርቶኒ እና በመርፌ ስሪንጅ በመገጣጠም የራሱ "ካሱ" የተባለ ኤክስካቫተር ለመስራት በቅቷል። ምስሉም ቪዲዩውም እንሆ
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) የታዳጊው የፈጠራ ውጤት ለሀገር የሚጠቅም ነው በማለት አፈላልገው አዲስ አበባ ድረስ አስመጥተው በመ/ቤታቸው የሚገኘውን የፈጠራ ላብራቶሪ እንዲመለክት አድርገውታል። ይህን የካሱን መልካም ጅምር ለማበረታት ሚ/ር መ/ቤቱ እያደረገ ያለው መልካም ተግባር ደግ የሚያሰኝ ነው።
Yes, God gives many gifts. The gift of healing for example. But do I need to travel to a specific place to experience those gifts? Do I need to know people who know certain “special” people so that Jesus would heal me? Do I have to give money so that I could get healed? Do I have to give money so that I will get back more?
I observe all these things when I watch some satellite ‘Christian’ TV programs in Africa. I have struggled with this topic for a long time but decided I could not keep my thoughts to myself. Television, like other media platforms can be used to share the gospel with many. But the effectiveness of the TV platform is limited as it is mainly one way communication. TV is very useful to broadly sow the gospel. You can add texting, phone calls and social media platforms to increase the effectiveness. But the problem is NOT using Christian TV, but it becomes a problem when you use Christian TV to replace the physical church. When you read a good book you get wisdom and information from the author. Even when the writer inspires you, in most cases it's impossible to consider the author your friend or your pastor. Because pastoral ministry is about shepherding the people known to the pastor. The satellite TV programs are often filling people’s minds with confused theology and spiritual practices. Often the Christian programs suggests that whatever you hear and see on TV, is what God is saying. But we should listen carefully. Sadly I see preachers on TV who have selfish desires to become idols themselves. They use the platform for selling almost everything. The first church in the book of Acts was known for:
Some years ago my friend invited me to an early Sunday morning service at his church. We finished the service around 10am and it was too early to go for lunch so he took me to another church that started 10:30am. I must admit I didn't listen to a single statement as my mind was full from the first service. I needed time to soak it in and reflect on it. After the second service we had lunch and my good friend suggested we attend an afternoon service in another church. I could not believe it. I declined. I see that same principle when I see people switching channel after channel to hear from God. How do you grow and become a disciple like that? What type of fruit do you bear? For me when a sinner, like me, comes to know God and becomes a child of God, that is a huge miracle. I am a miracle! I am a child of God. I don’t have to spend money to see a miracle. I don’t have to wait until my mobile number is mentioned. The greatest miracle was when God became Emmanuel, and showed His unfailing love through Jesus Christ. I love preaching the gospel to myself. If the gospel does not satisfy me, then nothing else would! Lee Strobel describes John 1:12 like this and I agree with him. Believe + Receive = Become a child of God John 1:12 Three things you can do
Share your story below. ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ይህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል በዓይምሮዬ ሲመላለስ ነበር። ክፍሉም የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ምዕራፍ 126 ሲሆን እንዲህ ይላል፣ 1 እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም። 2በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ። 3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን። 4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በነጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣ ምርኳችንን መልስ። 5በእንባ የሚዘሩ፣ በእልልታ ያጭዳሉ። 6ዘር ቋጥረው፣ እያለቀሱ የተሰማሩ፣ ነዶአቸውን ተሸክመው፣ እልል እያሉ ይመለሳሉ። አንዳንድ የመፅሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ይህ ዝማሬ እስራኤላውያን ከምርኮ በተመለሱ ጊዜ የተዘመረ እንደሆነ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ዝማሬ ንጉስ ዳዊት ልጁ አቤሴሎም በትረ ስልጣኑን በጉልበት ለመውሰድ በሞከረበት ጊዜ ሸሽቶ ከነበረበት ስፍራ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ የተዘመረ መዝሙር እንደ ሆነም የሚፅፉ አሉ። እናም የግጥሙ ፀሃፊ የደስታውን ሁኔታ በቁጥር አንድ ላይ "ህልም እንጂ እውን አልመሰለንም" ብሎ ይገልፀዋል። ይህም የእርስ በእርስ ዕልቂት፣ የጦርነት እና የምርኮ ስብራት ቶሎ የማይጠገን መሆኑን የሚጠቁም ነው። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እየሆነ ያለውን መንፈሳዊ፤ፖለቲካዊ እና ፈረጀ ብዙ ተሃድሶ ህልም እንጂ እውን አይመስልም ያስብላል። የአሜሪካው ድምፅ ጋዘጠኛ ሰለሞን የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባል እና የሰብአዊ መብት አክቲቪስት የሆነችውን ሶልያናን በአንድ ዲስያፖራ ስብሰባ ላይ (10ኛ ደቂቃ ላይ ማየት ይችላሉ) በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየሆነ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ጥያቄ ሲጠይቃት የመለሰችው መልስ “እያየን ያለነው ለውጥ ትንሽ ፈጣን ናቸው። ለመከታተልም ይከብዳል” የሚል ነበር። ሶልያና በብዙ የፍትህ ማጣት ችግር ያለፈች በመሆኗ አሁን እያየን ያለውን ሁኔታ የገለፀቸበት መንገድ ማጋነን አይሆንባትም። ምክንያቱም እንዳለችው እየሆነ ያለው ለውጥ እጅግ ፈጣን እና ለማመን ህልም የሚመስል ነው በመሆኑ ነው። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ከገቡበት ጊዜ እንስቶ ሁለቱም ህዝቦች አልቅሰዋል፤ለስደት ተዳርገዋል፤ ብሎም በሺዎች ሞተዋል። እኔም የማስታውሳቸው የጎረቤት ቤተሰብ ተለያይተዋል። ባል ኤርትራዊ፣ ሚስት ደሞ ኢትዮጵያዊ ሰለሆነች በጦርነቱ ጊዜ ባል እና ሚስት ተለያይተው እንዲኖሩ ምክንያት ሆኗል፤ ልጆቻቸውም እንዲሁ። ታዲያ በዚህ መራራ ታሪክ ውስጥ ብዙ ሲፀለይ ቆይቷል። እግዚአብሔርም ፀሎትን መልሷል። እንባም ታብሷል። አዲስ የሰላም ምዕራፍ ተከፍቷል። ይህ አዲስ መንፈስ በሁለቱም ሀገሮች ላይ እየነፈሰ ነው። ለዚህ ማሳያ በአስመራ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድን ሊቀበል የወጣው ህዝብ ምስክር ነው። የሚገባኝ ይህ ደስታ ዋጋ የተከፈለበት ደስታ መሆኑን ነው። ይህ በሀገር ላይ የፈሰሰው ደስታ ለብዙ ወጣቶች ስኬት መስፈንጠሪያ እንድሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም። በዚህ ደስታ ውስጥ ዐይኑ የተከፈተለት ብዙ ዕድሎችን ማየት ይችላል። ስለዕድሎቹ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ። በተፈጠረው የደስታ ድባብ ውስጥ አዲስ ነገሮች ለማየት የሚጠቅሙ ሶስት መርሆችን ልጥቀስና የዛሬውን ፅሁፌን ልጠቅልል።
ተጨማሪ••• ከ habeshastudent.com የተወሰደ
ምን አልባት የምለው ነገር ግር ያላችሁ እና የህይወት ጎዳና መራራ ናት የምትሉ በአጠቃላይ በቤታችሁ ሰላም ለናፈቃችሁ ከመርሆዎች ሁሉ በፊት ቀዳሚ የሆነውን የሰላም አለቃ ኢየሱስን ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ። ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “ሰላምን እተውላችኃለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኃለሁ፤እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም፡፡ ልባችሁ አይጨነቅ አይፍራም፡፡” እንድንፈራ እንድንጨነቅ የሚያደርገን ከበቂ በላይ የሆነ ምክንያት ሊኖረን ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በፊታችን ካለው ችግር የሚበልጥ ሰላምን ይሰጠናል፡፡ እርሱ ከሁሉ በላይ የሆነ ፈጣሪ እግዚአብሔር(አምላክ) ነው፤ እርሱ ለዘላለም ይኖራል፤ ፍጥረተ አለምን ሁሉ የፈጠረ ከሁሉ ነገር ጀርባ ሆኖ የሚቆጣጠር እርሱ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ኃያልነቱን ይዞ፣ እኛን እያንዳንዳችንን በጥልቀት ያውቀናል፤ በጣም ኢምንትና አናሳ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮቻችንን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሕይወታችን በሚገጥመን ነገሮች ሁሉ በእርሱ ብንታመን፣ ራሳችንንም በእርሱ ላይ ብናሳርፍ፣ ምንም እንኳን ከፈተናና ከችግሮች ጋር ብንጋፈጥም ያለ አንዳች ጉዳት እርሱ ይዞ ያሳልፈናል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህንን ነግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፡፡” እርሱ የሁሉ የመከራ ቁንጮ በሆነው ሞት ውስጥ አልፎ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል፡፡ በእርሱ የምንታመን ከሆነ በሕይወታችን በሚገጥሙን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እጃችንን ይዞ ይመራናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ እርሱ ከሞት እንደተነሳ ሁሉ በመጨረሻው ቀን በእርሱ የምናምን እኛን ከሞት እንደሚያስነሳንና ወደ ዘላለም ሕይወትም እንደሚወስደን ቃል ገብቶልናል፡፡ ኢየሱስን የበለጠ ለማወቅ ይህን ድህረ ገፅ ይክፈቱ። የችግር መፍትሄ የሚመነጨው ከግልሰብ እንጂ ከቡድን አይደለም በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ ልዩ የለውጥ ሞገድ እያየን እንገኛለን። ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ሚሊዮኖችን ያማለለ ንግግርን እና ዕቅዳቸውን ለህዝብ በማሰተዋወቅ ላይ ናቸው። ስልጣን ከያዙበት ቀን ጀምሮ እየተገበሩት ባለው ፈጣን የስራ ክንውን ከተማረኩት ሚሊየኖች ውስጥ አንዱ እኔ ነኝ። የዚህም ክንውኖች ቁንጮ የሆነው ሀገራዊ ዕርቅ እና የአንድነት ጥሪ ልዩ ስፍራ የተሰጠው ጉዳይ ሆኗል። ለዛሬ ግን የማካፍለው ሃሳብ ወጣቶችን በቡድን ሳይሆን በግል የማነቃቃት አስፈላጊነት ምክንያቶችን ስለማሳየት ይሆናል። በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ልዩ ልዩ የወጣቶችን እንቅስቃሴ እየተመለከትኩኝ ነው። አዲስቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ የሚለው በማህበራዊ ድህረ ገፅ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ጭምር የተሳተፉበት እንቅስቃሴ ልዩ ትኩርት ሰጥቼዋለው። ርዕሱ እጅግ የሚማርክ እና የጊዜው መልክት ነው ብዬ አምናለው። ይሁንና የሰማኋቸው ንግግሮች ሁሉ (ያልሰማኋቸው ደግሞ ንግግርች ደሞ ሊኖሩ ይችላሉ) በህብረ ቡድን መዋቅር ላይ የሚያተኩሩ ይመስላሉ። ይህ ማለት ወጣቶችን በአንድ ላይ በቡድን በቡድን የማየቱ ነገር ከፍ ያለ ስፍራ የተሰጠው ጉዳይ ሲሆን ይታያል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜና ላይ የተመረቁ ተማሪዎች ተደራጅተው የኮብል ስራ መስራት ጀመሩ የሚለውን ዜና ስሰማ በጣም ነው ማመን ያቃተኝ። ስራ መናቄ አይደለም። ማንም ሰው ራሱን ለመደገፍ የትኛውንም ስራ ትንሽ ወይም ትልቅ ሳይል መስራት አለበት። ነገር ግን ልቤን የከበደው “አራት አመት በዩንቨርስቲ የተማሩ ተማሪዎች ተድራጀተው” የሚለው አረፍተ ነገር ነው። ምክንያቱም እኔ ዜናውን የተረዳሁት ድህነቱ አስገድዷቸው አልያም ከመካከላቸው በተማሩበት ሙያ ሌላ ስራ እንዴት መስራት እንደሚችሉ ማየት አልቻሉም። ወይም ጥሩ በእድሜ የገፋ ጠቋሚ አልነበረም ብሎ ማሰብ ይቻላል። ሪፖርቱ በዛ መንገድ ቢቀርብ ኖሮ ጥሩ ትምህርት ይሆን ነበር። ነገር ግን የአራት ዓመት የከፈተኛ ትምህርት ግብ የኮብል መንገድ ስራ ላይ መደራጀት ከሆነ የትምህርት ተቋሙ ዓላማም ያጠያይቃል። ከዛ ባሻገር ሁሉ ነገር አንድ ለአምስት ተደራጅ፤ ቤት እንድትሰራ ተደራጅ፤ገንዘብ እንድትበደር ተደራጅ፤ ዲያስፖራው ይደራጅ የሚለው ሃሳብ እጅ እጅ ብሎኛል። በመሆኑም ይህ አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ የሚለው ሃሳብ “እኛ” ከሚለው ሃሳብ የሚያወጣ እና እያንዳንዱ ሰው በተሰጠው የህይወት ዘመን “የእኔ” ድርሻዬ ምንድ ነው? የሚለውን ሃሳብ ኢንዲያስብ ፍንጭ ይሰጣል ብዬ አስባለው። ይህን "አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ" የሚለው ከአባባል እና ከጊዜያዊ ዕርቅ የዘለለ መሆን አለበት። ስሜታችን ተስፋ ስለሞላው የሚቀየረው ስሜታችን ብቻ ነው። ነገር ግን ያ የግል ተስፋ በተግባር መልካም ዓላማን በማስፈፀም ሲለወጥ አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ የሚለው ትርጉም ያገኛል። ታሪክን ስንመለከት ቡድን እንደ ቡድን የማስፈፀም ቅልጣፌን እንጂ ችግር የመፍታት ግኝትን አያመነጭም። በቡድን የሚሰጥ የውሳኔ ሃሳብ አለ እንኳን ቢባል አንድ ግለሰብ ከቡድኑ ውስጥ ሃሳቡን መጀመሪያ ሊያፈልቅ ግድ ይላል። ለዚህ ብዙ ምሳሌ መስጥት ይቻላል ይህ ድህረ ገፅ ወደ መቶ የሚጠጉትን ግለሰቦች በሁሉም የህይወት ዘርፎች ዘርዝሮአቸዋል። ባህላችንን ያየን እንደሆነ የተለየ ሃሳብ አንወድም ወይም አናበራታታም። አንድ ሰው በሃሳቡ ቢለይ ይገለላል። በንግግር ውስጥ ክርክር ሲሆን ወድያው ወደ ግጭት እናመራለን። ምክንያቱም ሃሳቡን ከግለሰቡ ለይተን ማየት አንችልም። ይህ የሆነው ብዙ ነገራችን የጋራ ኑሮ ነው በግል ብዙ ሃሳብ የለንም። ነገር ሁሉ በዕቁብ እና በዕድር መሳይ ቡድኖች እንዲያልፍ ይፈለጋል። ይህ ደግሞ ሃሳቦችን ወደ መደጋገም እንጂ አዲስ መፍትሄ አፍላቂዎች አላደረገንም። አንዳንዴ ገጥሟችሁ አያቅም? ልዩ ሃሳብ ይዛችሁ የመንግስት ቢሮ ስትቀርቡ ይህ ጉዳይ አይታወቅም፤ ወይም አይመለከተንም፤ ኮሚቴው ተነጋግሮ ምላሾች ሊሰጥ ይችላል የሚሉ ምላሽ በብዛት ይሰተዋላሉ። ምላሽም በድፍረት የሰጡ ግለሰቦች ይበጠለጠላሉ። ለምሳሌ አርከብ ዕቁባይ በአዲስ አበባ ከነቲባነቱ ብዙ ለውጥ ያመጣ መሪ ነበር። ነገር ግን እንደምሰማው ነበረ የተባለውን ቡድን ሸፈነ መሳይ ምክንያት ተሰጥቶት ከስራው ገለል ተደርጓል። ወይም እርሱ ይህን ያን ቡድን አይወክልም በሚል ተፈርጆም ሊሆን ይችላል የተነሳው። ይህም የሆነው መሪዎች በቦታቸው ቡድንን ወክለው እንጂ በግል አምነውበት ላይሆን ይችላል አመራር የሚሰጡት ማለት ነው። ነገር ግን መሪዎች በግላቸው አቅም የተሰጣቸው እና የሰለጠኑ ቢሆኑ ኖሮ አዳዲስ ነገሮችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ስጋቶችን መጋፈጥ የሚችሉ ይሆኑ ነበር። የችግር የመፍትሄ ሃሳብ በቡድን አይመነጭም። ሃሳብን ማጎልበትም ሆነ መፈፀም ከማመንጨት ይለያል። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ይባል አይደል ተብዬ ልጠየቅ እችላለው። ነገር ግን ያ አባባል በኢትዮጵያኖች ሲመነጭ ዕድር ተኮር ችግሮችን ለምፈታት እንጂ ገብሬውን በበሬ ከማረስ አላሳረፈውም። ጠበአጭሩ ራዕይ ወይም የችግር የመፍትሄ ሃሳብ በቡድን አይመነጭም። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ይባል አይደል ተብዬ ልጠየቅ እችላለው። ነገር ግን ያ አባባል በኢትዮጵያኖች ሲመነጭ ዕድር ተኮር ችግሮችትን ለምፈታት እንጂ ገበሬውን በበሬ ከማረስ አላሳረፈውም። አንድ ጊዜ በገጠር የሚኖር ገበሬ ቄስ አያቴን ጥያቄ ጠየቁት። እስካሁን በሞፈር ቀንበር ስታርስ ለምን ይህን ነገር በሌላ አልቀይረውም ብልህ አስበህ ታውቃልህ ስለው የአያቴ ምላሽ ፈጣን ነበር። ለምን ብዬ አለኝ ምክንያቱም ሁሉም ገበሬ በዚህ ነው የሚያርሰው ብሎ ጨረሰው። አያችሁ የሱ አመለካከት የተቃኘው ተጋግዞ እርሻን ማረስ፤ ማረም እናም ደግሞ የለውን ትንሽ ነገር መከፋፈል እንጂ ተለይቶ የስራ ጫናውን የሚያቀልለትን ሃሳብ የሚያመንጭበት ዕድል ባህሉ አልፈቀደለትም። የተማርን ነን የምንለውም ያው ነን። በግላችን ባለን ዓላማ ሳይሆን የቡድን ሃሳቦች ይጨፈልቁናል። ችግርን ተቀብለን እንድንኖር አካባቢያችን ያስተምረናል። ጠ/ሚ ዶ/ር አብይን እንዲህ ፍንትው ብለው የወጡት የቡድን ሃሳብ ስለያዙ ሳይሆን የግላቸው ሃሳብ አጉልተው በማሳየታቸው ነው። የሁላችንንም ቀልብ ስበዋል። በመሆኑም ወጣቶች ምን በጋራ እንስራ ወይም ከማን ጋር ልስራ ብሎ ከመጠየቅ በፊት እኔ በግሌ ምን ላድርግ የሚለውን ጥያቄ ቢያስቀድሙ መልካም ነው። ይህ ጥያቄ ሲቀድም ወጣቶች በግላቸው አሰላለፋቸውን ማወቅ ይችላሉ። ከሌላውም ጋር እንዴት በሽርክና መስራት እንዳለባቸው ያውቃሉ። ይህን በሌላ ፁሁፍ እመለስበታለው። እኔ የተመረኩት በሐዋሳ ዩንቨርሲ ኮሚፒተር ሳንይንስ ነው። አስራ ሁለተኛ ክፍል ላይ ሳለው ነበር ምን መማር እና መስራት እንዳለብኝ ያወቁት። ትዝ ይለኛል የሚያበላ ትምህርት ተማር፤ ዶ/ር እገሌ ይህን ያህል ብር ይከፈለዋል አንተም እንደሱ ተምረህ ብር ታገኛለህ ተብዬ በተደጋጋሚ ተነግሮኛል። ነገር ግን ያን መንገድ አልሄድኩም። ብሎም በሙያዬ ወደ ማስበው የመንፈሳዊ አገልግሎት ስራ ለመጀመር ከ ኢትዩጵያ ቴሌኮሚንኬሽን ስለቅ ዕብድ ያለኝ ሰው ጥቂት የሚባል አልነበረም። ታዲያ ያኔ የሰዎችን ጫና ብሰማ ኖሮ ይህን ማድረግ የምችል ይምሰላችሁ ነበር? በፍፁም ለተገለጠልኝ ሃሳብ ራሴን ሰጠሁ አንድ ባንድ ነገሮች እያደጉ እያደጉ አሁን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ብዙ ሃገሮችን የድጅታል ስትራቴጂ ስራዎችን አመራር እሰጣለው። በዚህ ሂደት ውስጥ የጥቂት ግለሰቦች የሞራል ድጋፍ እና ፀሎት ትልቅ ደጀን ሆኖልኛል። የአንድ ግለሰብ ድምፅ ትልቅ አቅም አለው። ማስተጋባት ቀርቶ ተወዳዳሪ የሌለው ሃሳብ በግል እናመንጭ አስተውላችሁ ከሆነ የኢትዮጵያ የመንግስትም ሆነ የግል ሚዲያዎች ተደራሹ ቡድን ነው እንጂ ግለሰብ ሲሆን ብዙ ጊዜ አይታይም። ሁሌም ይህ ቡድን እንዴት ይሳተፍ፤ ይምጣ፤ ይቁም ነው እንጅ ስለ እኔ፤ አንተ፤ አንቺ የሚል ንግግር አሁንም ባዕድ ነው። ይህን ለማነፃፀር አንድ የምዕራብ ሚዲያ እና የኛን ሚዲያ የፖለቲከኞች የፖሊሲ አገላለፅ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ይህን የምለው ለማበላልጥ ሳይሆን ልዩነቱን በደንብ እንድታዩ ነው። ለምሳሌ በአሜሪካ አብዛኛው ህጎች ሲረቀቁ እንዴት አንድ ግለሰብን ይጠቅማሉ ወይም ይጎዳሉ በሚል ክርክር ይደርግባቸዋል። ያንንም ፖሊሲ ተጠሪ አንድ ግለሰብ ነው የሚሆነው። የአሜርካ ፕሬዘዳንቱ ጭምር አንዳንዴ የሚሰጡት ምሳሌ የአንድ ሰውን ታሪክ ውጤት የሚያሳዩ ናቸው። በመሆኑም ፖሊሲውን የሚሰማ ሁሉ እንዴት ያ አዲስ ፖሊሲ ተፅዕኖ እንደሚያሳድርበት ማወቅ ይችላል። በቅርቡ ደግሞ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የአርቲስት መሰረት መብራቴ ስም በመጥቀስ እንዴት የእርሷ ተሳትፎ በሁለተኛ ደረጃተማሪዎች ላይ መልካም ተፅዕኖ ሊያመጣ እንደሚችል ግሩም ምሳሌ አስቀምጠዋል። ይህ ችግር ምናልባት አንድ ሰው ውስጥ ያለውን አቅም ያለማወቅ አልያም የባህላችን መጥፎ ተፅኖ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ መደመር የሚለው ሃሳብ የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የተወደደ ሃሳብ ነው። እኔም አምንበታለሁ። ይህንንም ስል ስለ አንድነት እያሰብኩኝ እንደሆነ ይታሰብ። ነገር ግን መደመር ማለት የእኔ የግል እና ልዩ የሃሳብ መለያን ከሌላው ጋር መጨፍለቅ አይደለም። ይህ ማለት ቁጭ ብዬ የሚሆነውን መመልከት ማለት አይደለም። እንዲያውም እኔ በግሌ ምን ማድረግ እችላለው የሚለወን ጥያቄ በመጠየቅ ልዩ ልዩ የመፍትሄ ሃሳቦችን የማመንጨት ዕድል እንደተከፈተልኝ አያለው። መደመር የሚለው ለቡድን እና ብሔር ተኮር የሆነ አስተሳሰብን ለማስታረቅ ይጠቅማል ብዩ አስባለው። ነገር ግን የግል ሃሳብን አመሳስሎ መደመር ችግር ያመጣል። ይጨፈልቃል። የግለሰቦች መብትም ሊጣስ ይችላል ብዬ እሰጋለው። ስለዚህ መደመር የሚለው ቃል መዳረሻነቱ የግለሰብ ተሳትፎን የሚያጎለብት እንጂ የሚጨፈልቅ እንዳይሆን ልብ ሊባል ይገባል። ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ይህንን በፓርላማ መደመር ማለት መመሳሰል እንዳልሆን ማብራራታቸውን አስታውሳለው። ለስራ የማስፈፀም ሂደት ስንሰበሰብ ትኩረቱ በታወቀ ዓላማ እና የግል ተሳትፎ በግልፅ በተቀመጠበት ጉዳይ መሰባሰብ ብቅርቡ ወዳጆቼ እስቲ እንቀበጣጥር (brainstorming) እንዴት ሃገራችንን እንደምንጠቅም የሚል ግብዣ አቀረቡልኝ። ልቤ በጣም ደስ አለው። ቀጥዬም ጥያቄ አቀረብኩኝ ምንድ ነው ያሰባችሁት ነገር ወይም ራዕይ ወይም የታሰበ እቅጣጫ ብዬ ጠየኩኝ እናም መልሱ አይ አብረን እንድናፈልቀው ነው ተባልኩኝ። ይህ መተባባር ያለ ትኩረት አቅጣጫ የትም አያደርሰንም ነበር የኔ መልስ። እያንዳንዳችን ውስጥ ልዩ ተሰጦ እና አቅም አለ። ያንን ደግሞ ማወቅ፤ማሳደግ እና ሌሎች ሊከተሉት የሚቸሉት ሃስብ አድርጎ የማውጣት ሃላፊነት የዛው የግለሰቡ መሆን አለበት። መፅሐፍትን ማንበብ አጋዥ ጠቋሚ ግለሰቦችን ከጎን ማሰልፍ ለዚህ ዕገዛ ሊያደርግ ይችላል። በመጨረሻም የግል ሃሳቦች ተቀባይነት እያገኙ ሰዎች በጋራ የግል ሃሳብን የማንሸራሸር ልምድ ሲያሳድጉ ዘረኝነቱም ይቀንሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለው። ብዙ ሰው ስለ ብሔሩ ጭንቅ የሚለው የሚበላው የሚጠጣው በቡድን ሰለሆነ ነው ብዬ አስባለው። በቡድን ተራም ሆነ ቁም ነገር ሃሳቦች በዓይምሮ ይቀረፁና ግንፍል በሚለው ሲሜት አጀብ ተብሎ ስራ ሊሰራ ይሞከራል። ሳይሆን ደግሞ ሆ ተብሎ ለጥፋት ይወጣል። የግለሰብ ልዩ ልዩ ሃሳቦች ተጨፍልቀው ይደመሩና ብዙ የመፍትሔ ሃሳቦች ያለምንም ጥቅም ወደ አፈር ይወርዳሉ።
አደገኛ እና ጎጂ የግል ሃሳብችም ይኖራሉ። እነዚህንም በተቻለ መጠን ሃሳቡን ከግለሰቡ በመለየት የመቋወም ባህላችንን ማሳደግም ሌላው ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው። ሌላውን በሚቀጥለው ፅሁፍ ላቅርብ••. ለረዥም ፁሁፍ እና የፊደል ግድፈት ይቅርታ እየጠየኩኝ እስቲ ምን ትላላችሁ የግላችሁ ሃሳብ በሐገር ላይ ምን ፋይዳ ሊኖረው ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? እንደ ግለሰብ ይህን የምትግልፁብትስ መድረክ ልምዳቹ ምን ይመስላል። ከእያንዳንዳችሁ ለምስማት እናፍቃለው |
AuthorMiheret T. Eshete Archives
September 2024
Categories
All
|