ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ይህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል በዓይምሮዬ ሲመላለስ ነበር። ክፍሉም የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ምዕራፍ 126 ሲሆን እንዲህ ይላል፣ 1 እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም። 2በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ። 3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን። 4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በነጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣ ምርኳችንን መልስ። 5በእንባ የሚዘሩ፣ በእልልታ ያጭዳሉ። 6ዘር ቋጥረው፣ እያለቀሱ የተሰማሩ፣ ነዶአቸውን ተሸክመው፣ እልል እያሉ ይመለሳሉ። አንዳንድ የመፅሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ይህ ዝማሬ እስራኤላውያን ከምርኮ በተመለሱ ጊዜ የተዘመረ እንደሆነ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ዝማሬ ንጉስ ዳዊት ልጁ አቤሴሎም በትረ ስልጣኑን በጉልበት ለመውሰድ በሞከረበት ጊዜ ሸሽቶ ከነበረበት ስፍራ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ የተዘመረ መዝሙር እንደ ሆነም የሚፅፉ አሉ። እናም የግጥሙ ፀሃፊ የደስታውን ሁኔታ በቁጥር አንድ ላይ "ህልም እንጂ እውን አልመሰለንም" ብሎ ይገልፀዋል። ይህም የእርስ በእርስ ዕልቂት፣ የጦርነት እና የምርኮ ስብራት ቶሎ የማይጠገን መሆኑን የሚጠቁም ነው። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እየሆነ ያለውን መንፈሳዊ፤ፖለቲካዊ እና ፈረጀ ብዙ ተሃድሶ ህልም እንጂ እውን አይመስልም ያስብላል። የአሜሪካው ድምፅ ጋዘጠኛ ሰለሞን የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባል እና የሰብአዊ መብት አክቲቪስት የሆነችውን ሶልያናን በአንድ ዲስያፖራ ስብሰባ ላይ (10ኛ ደቂቃ ላይ ማየት ይችላሉ) በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየሆነ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ጥያቄ ሲጠይቃት የመለሰችው መልስ “እያየን ያለነው ለውጥ ትንሽ ፈጣን ናቸው። ለመከታተልም ይከብዳል” የሚል ነበር። ሶልያና በብዙ የፍትህ ማጣት ችግር ያለፈች በመሆኗ አሁን እያየን ያለውን ሁኔታ የገለፀቸበት መንገድ ማጋነን አይሆንባትም። ምክንያቱም እንዳለችው እየሆነ ያለው ለውጥ እጅግ ፈጣን እና ለማመን ህልም የሚመስል ነው በመሆኑ ነው። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ከገቡበት ጊዜ እንስቶ ሁለቱም ህዝቦች አልቅሰዋል፤ለስደት ተዳርገዋል፤ ብሎም በሺዎች ሞተዋል። እኔም የማስታውሳቸው የጎረቤት ቤተሰብ ተለያይተዋል። ባል ኤርትራዊ፣ ሚስት ደሞ ኢትዮጵያዊ ሰለሆነች በጦርነቱ ጊዜ ባል እና ሚስት ተለያይተው እንዲኖሩ ምክንያት ሆኗል፤ ልጆቻቸውም እንዲሁ። ታዲያ በዚህ መራራ ታሪክ ውስጥ ብዙ ሲፀለይ ቆይቷል። እግዚአብሔርም ፀሎትን መልሷል። እንባም ታብሷል። አዲስ የሰላም ምዕራፍ ተከፍቷል። ይህ አዲስ መንፈስ በሁለቱም ሀገሮች ላይ እየነፈሰ ነው። ለዚህ ማሳያ በአስመራ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድን ሊቀበል የወጣው ህዝብ ምስክር ነው። የሚገባኝ ይህ ደስታ ዋጋ የተከፈለበት ደስታ መሆኑን ነው። ይህ በሀገር ላይ የፈሰሰው ደስታ ለብዙ ወጣቶች ስኬት መስፈንጠሪያ እንድሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም። በዚህ ደስታ ውስጥ ዐይኑ የተከፈተለት ብዙ ዕድሎችን ማየት ይችላል። ስለዕድሎቹ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ። በተፈጠረው የደስታ ድባብ ውስጥ አዲስ ነገሮች ለማየት የሚጠቅሙ ሶስት መርሆችን ልጥቀስና የዛሬውን ፅሁፌን ልጠቅልል።
ተጨማሪ••• ከ habeshastudent.com የተወሰደ
ምን አልባት የምለው ነገር ግር ያላችሁ እና የህይወት ጎዳና መራራ ናት የምትሉ በአጠቃላይ በቤታችሁ ሰላም ለናፈቃችሁ ከመርሆዎች ሁሉ በፊት ቀዳሚ የሆነውን የሰላም አለቃ ኢየሱስን ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ። ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “ሰላምን እተውላችኃለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኃለሁ፤እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም፡፡ ልባችሁ አይጨነቅ አይፍራም፡፡” እንድንፈራ እንድንጨነቅ የሚያደርገን ከበቂ በላይ የሆነ ምክንያት ሊኖረን ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በፊታችን ካለው ችግር የሚበልጥ ሰላምን ይሰጠናል፡፡ እርሱ ከሁሉ በላይ የሆነ ፈጣሪ እግዚአብሔር(አምላክ) ነው፤ እርሱ ለዘላለም ይኖራል፤ ፍጥረተ አለምን ሁሉ የፈጠረ ከሁሉ ነገር ጀርባ ሆኖ የሚቆጣጠር እርሱ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ኃያልነቱን ይዞ፣ እኛን እያንዳንዳችንን በጥልቀት ያውቀናል፤ በጣም ኢምንትና አናሳ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮቻችንን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሕይወታችን በሚገጥመን ነገሮች ሁሉ በእርሱ ብንታመን፣ ራሳችንንም በእርሱ ላይ ብናሳርፍ፣ ምንም እንኳን ከፈተናና ከችግሮች ጋር ብንጋፈጥም ያለ አንዳች ጉዳት እርሱ ይዞ ያሳልፈናል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህንን ነግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፡፡” እርሱ የሁሉ የመከራ ቁንጮ በሆነው ሞት ውስጥ አልፎ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል፡፡ በእርሱ የምንታመን ከሆነ በሕይወታችን በሚገጥሙን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እጃችንን ይዞ ይመራናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ እርሱ ከሞት እንደተነሳ ሁሉ በመጨረሻው ቀን በእርሱ የምናምን እኛን ከሞት እንደሚያስነሳንና ወደ ዘላለም ሕይወትም እንደሚወስደን ቃል ገብቶልናል፡፡ ኢየሱስን የበለጠ ለማወቅ ይህን ድህረ ገፅ ይክፈቱ። Comments are closed.
|
AuthorMiheret T. Eshete Archives
February 2023
Categories
All
|