መቼም በፌስቡክ ላይ ብዙ አይነት ነገሮችን ከሰሞኑ እንመልከታለን። በዚህ የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ቀልቤን ከሳበው ትልቅ ነገር የካሱ ገረመው ፎቶ ነበር። ይህ ብላቴኔ በኮንሶ የሚኖር ታዳጊ ሲሆን በሰፈሩ ከኮንሶ ያቤሎ የመንገድ ስራ ላይ ኤክስካቫተር፤ ግሬደር እና ገልባጭ መኪኖችን በመንገድ ስራ ሲመላለሱ ተመልከተ። በዓይምሮው እሱ ምን መስራት እንድሚችል በመረዳት ኤክስካቫተር በካርቶኒ እና በመርፌ ስሪንጅ በመገጣጠም የራሱ "ካሱ" የተባለ ኤክስካቫተር ለመስራት በቅቷል። ምስሉም ቪዲዩውም እንሆ
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) የታዳጊው የፈጠራ ውጤት ለሀገር የሚጠቅም ነው በማለት አፈላልገው አዲስ አበባ ድረስ አስመጥተው በመ/ቤታቸው የሚገኘውን የፈጠራ ላብራቶሪ እንዲመለክት አድርገውታል። ይህን የካሱን መልካም ጅምር ለማበረታት ሚ/ር መ/ቤቱ እያደረገ ያለው መልካም ተግባር ደግ የሚያሰኝ ነው።
Comments are closed.
|
AuthorMiheret T. Eshete Archives
February 2023
Categories
All
|